About Us
   MWUD Profile
   Vision & Mission
   Photo Gallery
   Contact Information
   Feedback


  Institutions Under the Ministry
   Construction Works Coordinating Bureau
   Ethiopian Roads Authority
Federal Urban Planning Coordinating Bureau
   Land & Housing Coordinating Bureau
   Office of the Road Fund
   Policy, Research & Planning Coord. Bureau
   Agency for Goverment Houses
   Support Services Coordinating Bureau
   Urban Development Capacity Building Office


  Policies, Plans, & Packages
   National Urban Development Policy
   PASDEP
   Urban Industry and Development Package
   Urban Good Governance Reform Package
   Strategic Plan
   Annual Action Plan

 Home News & Articles Press Releases
  Press Releases

 

በተጠናከረና በተቀናጀ የመንገድ ጥገናና የትራፍክ ደህንነት የአገራችን የኢኮኖሚ እድገት ይረጋገጣል!

     መንገድ በአንድ አገር ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊና ፖለቲካዊ እንቅስቃሴ ውስጥ ጉልህ ሚና ከሚጫወቱት መሰረተ ልማቶች አንደኛውና ዋነኛው ነው፡፡ አገራችንም በፍጥነት ከድህነት ተላቃ መከከለኛ ገቢ ካላቸው አገሮች ተርታ ለመቀላቀል እንድትችል፣ አሁን ባለው ተጨባጭ ሁኔታ የኢኮኖሚያችን የጀርባ አጥንት የሆነውን የግብርና ምርታችን በፍጥነት ወደ ገበያ ለማቅረብ፣ ለታዳጊው ኢንዱስትሪያችን ጥሬ ዕቃነት የሚውሉትን ምርቶች በፍጥነት ወደሚፈለገው ቦታ ለማድረስ፣ እንዲሁም ለግብርናው ግብዓት የሚሆኑትን የኢንዱስትሪ ውጤቶች ለአርሶአደሩ ለማቅረብ በአጠቃላይ ልማታችንን ለማፋጠን  በሚደረጉት እንቅስቃሴዎች ውስጥ መንገድ የሚጫወተው ሚና ከፍተኛ ነው፡፡

የኔፓል የልዑካን ቡድን የሥራ ጉብኝት አደረገ

 በኔፓል የአካባቢ ልማት ምክትል ሚኒስትር የተመራ የልዑካን ቡድን ከታህሣሥ 6 እስከ ታኀሣሥ 12 ቀን 2002 ዓ.ም. ለሰባት ቀናት በፌደራላዊ አወቃቀር፣ በከተሞች ድህነት ቅነሳና መልካም አስተዳደር ዙሪያ በአዲስ አባባ ፣አዳማ፣ አዋሳ እና ይረጋለም ከተሞች በመዘዋወር የልምድ ልውውጥና የመስከ ጉብኝት አደረገ፡፡

ኢትዮጵያ በቴክኖሎጂ ሽግግር ባስመዘገበችው የላቀ አፈፃፀም የ2ዐዐ9 ብቸኛ ተሸላሚ ሆነች

ኢትዮጵያ በቴክኖሎጂ ሽግግር ረገድ የአግሮስቶን ቴክኖሎጂን ወደ አገር ውስጥ በማስገባትና በማስተዋወቅ ብሎም በአጭር ጊዜ ውስጥ ቴክኖሎጂውን በማስፋፋት በወሰደችው ግምባር-ቀደም እርምጃና ባስመዘገበችውም ከፍተኛ ውጤት የደቡብ-ደቡብ ዓለምአቀፍ የሀብትና የቴክኖሎጂ ልውውጥ ማዕከል /South-South Global Assets & Technology Exchange (SS-GATE)/ የተባለ አለምአቀፍ ድርጅት እ.ኤ.አ ከሰኘቴምበር 3-4 ቀን 2009 ዓ.ም. በቻይና ሻንጋይ ከተማ ባካሔደው ኮንፈረንስ በቴክኖሎጂ ሽግግር፣ የመኖሪያ አካባቢ በማሻሻልና በሥራ ዕድል ፈጠራ የ2009 ብቸኛ ተሻላሚ አድርጓታል፡፡

በመከላከያ ሠራዊታችን የተሳካ ተልዕኮ ኮርተናል!

ከሁለት ዓመታት በፊት የሶማሊያ አሸባሪ ኃይሎችና ተባባሪያቸው በአገራችን ያለውን ሰላምና የልማት እንቅስቃሴ ለማደናቀፍ ከፍተኛ እንቅስቃሴ በጀመሩበት ወቅት ይህንን የፀረ-ሰላምና ፀረ-ልማት ተልዕኮ በማክሸፍ የኢትዮጵያን ደህንነትና ጥቅም የማረጋገጥ ኃላፊነት የተሰጠው ለመከላከያ ሠራዊታችን እንደነበር የሚታወስ ነው፡፡

የከተማ ልማትና መልካም አስተዳደር ፕሮግራሞች

የሥራና ከተማ ልማት ሚኒስቴር ከክልሎች ጋር በቋሚነት በየሶስት ወሩ የዕቅድ አፈጻጸም ግምገማና የምርጥ ተሞክሮ ልውውጥ ያደርጋል፡፡ በዕቅድ አፈጻጸም ላይ ባጋጠሙ ችግሮች ዙሪያም በስፋት ይወያያል፡፡ ለችግሮቹም በጋራ የመፍትሔ ሐሳቦችንም ያስቀምጣል፡፡
 

መንግሥት የመጠለያ ችግሮችን ለመፍታት የጀመራቸውን ፕሮግራሞች አጠናክሮ ይቀጥላል

የዓለም የመጠለያ ቀን በዓመቱ እ.ኤ.አ. በኦክቶበር የመጀመሪያው ሰኞ እንዲከበር የተባበሩት መንግሥታት በወሰነው መሰረት ዕለቱ በዚህ ዓመት ሕብራዊ ከተሞች /harmonious cities/ በሚል መልዕክት በየአገሩ ይከበራል፡፡ መልዕክቱ በተባበሩት መንግሥታት የተመረጠበት ዋነኛው ምክንያት በከተማ ልማቱ ዘርፍ በኢኮኖሚው፣ በአካባቢ ጥበቃ፣ በማህበራዊ አኗኗር ወዘተ የነዋሪዎች ሕብር አስፈላጊነትን ለሁሉም ለማስገንዘብ ነው፡፡ 

   LEGISLATION    NEWS & ARTICLES    DOWNLOADS    ANNOUNCEMENTS
  Proclamations
  Acts
  Directives

  News & Events
  News search
  Press releases
  Articles
  Publications
  Other resourses

  Tender notice
  Vacancies

Copyright © MWUD. All Rights Reserved.
Site Developed by Cybersoft

Home | News | Webmaster | Site map | Feedback