| |
|
የመንገድ ፈንድ በመደበው ገንዘብ ከ32,022 ኪሎ ሜትር በላይ መንገድ ተጠገነ
የኢትዮጵያ መንገድ ፈንድ በመደበው 1.3 ቢሊዮን ብር ወጪ 32,022 ኪሎ ሜትር መንገድ በፌዴራልና በክልል የመንገድ ባለሥልጣን መሥሪያ ቤቶች አማካኝነት መጠገኑ አስታወቀ፡፡ ለመንገድ ጥገና የሚያስባስበውን ፈንድ ለማሳደግም ጥረት በማድረግ ላይ እንደሚገኝ ገልጿል፡፡
|
|
ጥቂት ስለከተማ ፕላን
ከተማ የሚለው ቃል ትርጉም ከአገር አገር የሚለያይ ሲሆን ሁሉም እንደ አገሩ ተጨባጭ ሁኔታ መሥፈርት ያወጣለታል፡፡ በከተማ ፕላን አዋጅ ቁጥር 574/2000 በተደነገገው መሠረት በኢትዮጵያ ውስጥ ከተማ ማለት “ማዘጋጃ ቤት የተቋቋመበት ወይም ከ2,000 ወይም ከ2,000 በላይ የሕዝብ ቁጥር ያለውና ከዚህ ውስጥ 50% የሚሆነው የሰው ኃይል ከግብርና ውጭ በሆነ ሥራ የተሰማራ ሆኖ የሚገኝበት አካባቢ ነው፡፡” ይህንን መሥፈርት ግንዛቤ ውስጥ በማስገባት በኢትዮጵያ ውስጥ ከ900 በላይ ከተሞች ያሉ ሲሆን እነዚህም በአብዛኛው በኦሮሚያ፣ በአማራ፣ በደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና በትግራይ ክልሎች የሚገኙ ናቸው፡፡
|
|
የከተማው ፈርጦች
የግለሰብ ቤት ተከራይቼ የምኖር በመሆኑ ሰርቼ በወር የማገኘው ገንዘብ አብዛኛውን ለቤት ኪራይ ነበር የማውለው፡፡ በመሆኑም ይህ ሁኔታ ኑሮዬን እጅግ አክብዶብ" እንደነበር አስታውሳለሁ፡፡ ከአምስት ዓመታት በፊት መንግሥት የመኖሪያ ቤት የሌላቸው የአዲስ አበባ ነዋሪዎች የጋራ መኖሪያ ቤት /ኮንዶሚኒየም/ ተጠቃሚ ለማድረግ አስቦ በየቀበሌው ተመዝገቡ የሚል ማስታወቂያ ሲወጣ ነገሩ እውነት ባይመስለኝም ተመዘገብኩ፡፡
|
|
“ቤቶቹ ተጠናቅቀው ለተጠቃሚዎች በመተላለፋቸው በጣም ተደስቻለሁ”፡
“ያሰቡት ከግብ ሲደርስ የተመኙት ሲሳካ የወለዱት ለቁምነገር ሲበቃ፣ ያቀዱት ሲፈፀም” እንደማየት የሚያረካ ነገር የለም ቢባል ማጋነን አይሆንም፡፡ የኮንዶሚኒየም ቤት በዚህ ሀገር ተገንብቶ የዝቅተኛውን ህብረተሰብ የመኖሪያ ቤት ችግር ያቃልላል ብሎ ማሰብ እራሱ የማይወጡትን ተራራ የሞመከር ያህል ነው የሚመስለው፡፡ ይሁን እንጂ የማይወጡትን ተራራ በመውጣት ሞክሮ ውጤታማ መሆን ደግሞ እጅግ አስደሳች ነው፡፡
|
|
የመንገድ ግንባታና የአገር ውስጥ የሥራ ተቋራጮች
የሀገሪቱን ገጠር በሚያስተሳስር መልኩ እየተሠሩ ያሉት የመንገድ አውታሮች ተስፋ ሰጪና የፈጣን ልማት ግቡን የሚያግዙ ሆነዋል፡፡ የአገሪቱን ፈጣን ዕድገት ከማረጋገጥ አኳያ የሚሠሩት መንገዶች የሥራ አጥነት ችግሮችንም በመቅረፍ ረገድ ትልቅ ሚና እየተጫወቱ እንደሆነ የዘርፉ ሪፖርቶች ይጠቁማሉ፡፡
|
|
“የድልድይዩ መሠራት የኢትዮጵያና የጃፓን ሕዝቦችን ግንኙነት ይበልጥ ያጠናክረዋል"
በ1998 ዓ.ም. ግንባታው የተጀመረውና በዘመናዊ መልክ ሲሠራ የቆየው አዲሱ የአባይ ድልድይ ጳጉሜን 5 ቀን 2000 ዓ.ም. ይመረቃል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ በአይነቱ ከምስራቅ አፍሪካ የመጀመሪያው ይሆናል ተብሎ የተገመተው አዲሱ የአባይ ድልድይ ከአዲስ አበባ 205 ኪሎ ሚትር ርቀት ላይ ይገኛል፡፡ የድልድዩ ግንባታ ከመሬት ጠለል በላይ 1ሺ 71 ሜትር ከፍታ አለው፡፡ ጠቅላላ ርዝመቱ 303 ሜትር ሲሆን ጥገናዎችን አየተካሄዱበት እስከ 100 ዓመታት ያለምንም ችግር የማገልገል አቅም እንዳለው ግንባታውን ያካሄዱት ባለሙያዎች ይገልፃሉ፡፡
|
|
An Overview of the Historical Evolvement of Construction Works Regulatory Bodies in Ethiopia
In Ethiopia, the regulatory body of construction sector has undergone various organizational changes under different governments.
Though legally regulated modern construction works in Ethiopia was started four decades ago, the history of construction works has passed many centuries. As regarded to legality, formally controlled construction works began in the country with the establishment of the Ministry of Public Works by Order No. 38 of 1964, with the mandate to regulate the government construction sector. At that time, local and private construction firms were encouraged to engage in the construction industry and special back-ups and incentives were given to build the capacity of local contractors to participate in joint ventures and international construction bids.
|